መለኮትነት

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የፌስቡክ መድረክ፡ ስለድንግል ማርያም፡ እግዚአብሔራዊና መለኮታዊ ማንነትና ምንነት፥ ፈጣሪነትም አስመልክቶ፡ ለቀረበ ጥያቄ፡ የተሰጠ ምላሽ።

በፌስቡክ፡ ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የቀረበ ሥዕላዊ መግለጫ፦

     "መርዓተ አብ!" ወይም፡ "የአብ ሙሽሪት!" የእግዚአብሔር አብ ሙሽሪትና የእግዚአብሔር ልጁ፡ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የኾነችው፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡ በዚህ ብቅዓቷ፡ የፈጣሪዋ፡ የክብሩ ብቻ ሳይኾን፡ በአምልኮቱም፡ የእርሱ ተካፋይ ኾናለች።

ሥዕሉን ለመመልከት!... 

ከአቶ ሠመረ ገብረ-መስቀል የቀረበ ጥያቄ፦

     በኣምልኮትም የእርሱ ተካፋይ ሁናለች ማለት ምን ማለት ነው??? ኣልገባኝም ኣብራሩልን!