መንፈስ፣ መንፈስ-ቅዱስ፣ መንፈስ-ርኩስ፣ ዕፀ-በለስ። ፳፱ ኅዳር ፪ሺ፱ ዓ.ም. (08 December 2016)

"መንፈስ፣ መንፈስ-ቅዱስ፣ መንፈስ-ርኩስ" በተመለከተ: ከኪዳናዊ ዮሓንስ ደጉ የደረሰን ፪ተኛ እጦማር።

በመስከረም ወር: ኪዳናዊ ዮሓንስ ደጉ: "መንፈስ፣ መንፈስ-ቅዱስ፣ መንፈስ-ርኩስ" በሚል ርእስ ያቀረበውን የምርምር ጽሁፍ: በኅዋ ስሌድችንና በፌስ ቡክ መድረካችን ላይ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ ለዚሁ የምርምር ጽሁፍ የማሟያ መልስ: ከኢትዩጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት የተሰጠውን ሰፊ ማብራሪያ ጽሁፍ: እንዲሁ ለአንባቢዎቻችን ለንባብ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡

ኪዳናዊ  ዮሓንስ ደጉ: ሌላ ተጨማሪ ፪ተኛ ቀጣይ ምርምር አካኺዶ ያዘጋጀውን መልእክት: እንዲሁም:  ለዚሁ ጽሁፍ: ለ፪ኛ ጊዜ:  ከኢትዩጵያ የእግዚአብሔር መንግሥት የተሰጠውን የድጋፍና የማብራሪያ መልእክት፡ እናንተ እድምተኞቻችን አንብባችሁ ቁምነገር እንደምትገበዩበት በማመን: በቅደም ተከተል አቅርበንላችኋልና ተመልከቱት፡፡