በዓለ ትንሣኤ፥ ፋሲካ፥ ጣዖት አምላኪ፥ በኵር፥ የፋሲካ በግ፥ ለንጊኖስ፥ ምልጣን፥ ማዕዶት፥ ዳግማዊ ትንሣኤ፥ ሰንበት፥ ቅዳሜ ስዑር፥ አቤሜሌክ፥ በዓለ ዕርገት፥ ርክበ ካህናት፥ በዓለ ሃምሳ:: ሚያዝያ ፪ ቀን፡ ፪ሺ፲፪ ዓ.ም. (10/April/2020)

እንኳን፡ ለ፪ሺ፲፪ (፳፻፲፪)ኛው ዓመተ ምሕረት፡ በዓለ ትንሣኤ: በያለንበት አደረሰን!

ይደረስ፦ በምድርና በሰማያት በመላችው፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዕቅፍ ውስጥ፡ የእግዚአብሔርና የኢትዮጵያ ልጆች፣ ነጋሢዎችና ካህናት ኾናችሁ፡ "ኢትዮጵያ" በተባለችው የዐፅመ ርስት አገራችሁ ሠፍራችሁ፥ በኪዳናዊው ኢትዮጵያዊ የጨውነት ህልውናችሁና የመብራትነት ተልእኳችሁም፡ አልጫና ጨለማ በኾነው፡ በዓለሙ ኹሉ አህጉራት፡ በመለኮታዊው ዕቅድ ተዘርታችሁና ተሠራጭታችሁ፣ ተልካችሁና ተመድባችሁ፡ በቀዳማዊቷ የትንሣኤና በዘለዓለማዊቷ የሰንበት ሕይወት ለምትኖሩ፡ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ወገኖቻችን ለኾናችሁት፡ ኪዳናውያን ወንድሞችና ኪዳናውያት እኅቶች ኹሉ! በያላችሁበት!

በእግዚአብሔር አብወእም ድንግል ማርያም፥ በእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስም ኢትዮጵያዊዉን ሰላምታችንን፡ እናቀርብላችኋለን።