በደቡብ አፍሪቃ አገር

በደቡብ አፍሪቃ አገር፡ በኢትዮጵያውያትና በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ስላለው አሠቃቂ ግፍ፡ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል።

በአኹኑ ሰዓት፡ በደቡብ አፍሪቃ አገር፡
በኢትዮጵያውያትና በኢትዮጵያውያን ላይ፡
እየደረሰ ስላለው ሰቆቃ፡
ተጠያቂው ማን ነው? መፍትሔውስ ምንድር ነው?

ይህንኑ አስመልክቶ፡ በኢትዮጵያውያትና በኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ አኹንም፡ የ''እግዚኦታ'' እና ''ፈኑ እዴከ እምአርያም!''፡ ማለትም፡ ''እጅህን ከአርያም ላክ!''፩  የሚሉ፡ አሳፋሪና ዓመፀኛ ጸሎቶችና ልመናዎች፥ ምልጃዎችና ምሕላዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።