ነሐሴ ፲፮ ቀን፥ ፳፻፯ ዓ.ም (22 August 2015)

የ፳፻፯ ዓ.ም. የፍልሰታ ማርያም በዓል መልእክት።

አግሃደት ፍልሰታሃ፡ ማርያም ድንግል!
በከመ ትንሣኤ ወልዳ፡ ዘልዑል!

ድንግል ማርያም፡ ፍልሰቷን ገለጠች!
የልጇን ትንሣኤ፡ በእርሱ አጸደቀች!

+ + +

ልዑል እግዚአብሔር፡
ሃይማኖታችንና አገራችን፥ እናታችንና ንግሥታችን፡
እግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡
ከምድር ወደሰማያት የገባችበትን፡ የፍልሰቷን በዓል፡
ዘንድሮም፡ በ፳፻፯ተኛው (ኹለት ሽህ፡ ሰባተኛው) ዓመተ-ምሕረት፡
በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡
እንኳን፡ በሰላም ለማክበር አበቃን!

+ + +

ፍልሰታሃ ለማርያም!

ድንግል ማርያም፡
በመለኮታዊና ትስብእታዊ የተዋሕዶ ኹለንተናዋ፡
ወደሰማያት የመውጣቷ ትንግርት!

ሰማያዊ ልዕልና፡ ዘበዓለ ፍልሰታ ለማርያም።