አኀዛት

ስለፊደላትና አኀዛት ሆህያት ጥንቃቄ ማሳሰቢያ።

ለክቡራትና ለክቡራን አንባቢዎቻችን፡
አጭር ማሳሰቢያ።

    በዚህ የኅዋ ገጻችን ላይ ሠፍረው የሚነበቡት ጽሑፎች ኹሉ፡ በግእዙና በኢትዮጵያኛው ቋንቋዎች ተከትበው የሚቀርቡ በሚኾኑበት ጊዜያት፡ ቃላቱና አኀዛቱ፡ በራሳቸው ፊደላትና ቍጥሮች ብቻ ተከናውነው መዘጋጀት እንደሚገባቸው፡ እሙን ነው። ይህን አመኔታ፡ ኢትዮጵያዊው፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ሥርዓት፡ አበክሮና አጠንክሮ ያመለክተዋል።