ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት፡ የምስጋና ጸሎት።

የኢትዮጵያ ልጆች፡ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት፡ የምስጋና ጸሎት።

አባታችንና እናታችን፥ እኅታችንና ወንድማችን፥ መንፈሳችንም፡ እግዚአብሔር ሆይ!

አቤቱ እንቀድስሃለን እናመሰግንሃለንም፤ አቤቱ እናወድስሃለን፤ እንታመንብሃለን፤ አቤቱ እናገንሃለንም፤ ለቅዱስ ስምህ እንታዘዛለን፣ እንሰግድልሃለን፤ ጕልበት ኹሉ፡ ለአንተ ይሰግዳል፤ አንደበትም ኹሉ፡ ወደአንተ ይጮሃል።

አንተ፡ የአማልክት አምላክ ነህ፤ የገዢዎች ገዢ ነህ፤ የንጉሦችም ንጉሥ ነህ። አንተ፡ የሥጋዊው ኹሉ፥ የነፍሳዊዉም ኹሉ ወገን ፈጣሪ ነህ።

ልጅህ እግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕ፡ "እናንተ ስትጸልዩ፡