ኣጼ ቴዎድሮስ መጋቢት ፯ ቀን፡ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (16 March 2017)

ከኪዳናዊ ዮሓንስ ደጉ፡ እንዲኹም፡ ከሀኪም ዘርፉ መላኩ፡ ስለአጼ ቴዎድሮስ የቀረበ መጠይቃዊ አስተያየት።

ይድረስ፦ ለተወደዳችኍ ኪዳናውያን ወንድሞቼ፡ ዮሴፍና ኤርምያስ [ንቡረ-እድ፣ ዘኣኵስም ጽዮን]።

ለውብና መልካም ሥነ-ፍጥረቱ፡ ፈጣሪያችንን እግዚኣብሔርን ከኹሉ ኣስቀድሜ ኣመስግናለሁ! ከመላው የቤተሰቦቻችኍ ኣባላት ጋር በኪዳናዊው ደኅንነት ተጠብቃችኍ፡ በመልካም ደስታና ሓሤት እንደምትገኙ ኣምናለሁ!

እነዚያን የመሰሉ፣ መልካም ዕውቀት የሚገኝባቸውን ጽሑፎች ኣቅርባችኍ፡ መልካም ዕውቀት እንዳገኝና እንድደሰት ስላደረጋችኁኝ ደስ ብሎኛል! እግዚኣብሔር ይስጥልኝ! ጽሑፎቹን ከኅዋ ሰሌዳው ላይ እንድመለከታቸው የጋበዘኝ፡ ኪዳናዊ ዘርፉ ነው፤ እርሱንም በዚህ ኣጋጣሚ እግዜር ይስጥልኝ! ማለት እፈልጋለኁ።