እግዚአብሔር እም ድንግል ማርያም

ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፯ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ሰባተኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡ ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

ልዑል እግዚአብሔር፡
እንኳን፡ ለ፳፻፯ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] ሰባተኛው)
ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡
በያለንበት፡በደኅና አድርሶ፡
ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

+ + +

መግቢያ

እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥና በመላው ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ ይህን ከመሰለው የጾምና ጸሎት ሱባዔያችን የተነሣ፡ እነሆ፡ ከዚሁ ጊዜ ለመድረስ አብቅቶናል፤ ስለዚህ፡ ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምሕላ ጸሎታችን፡ ልንፈጽማት ይገባናል።

ሴትነት፡ በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነት።

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት
ኪዳናዊ ሕይወት፡
"ሴትነት"።