ወረቦች (የሽብሸባ ዝማሬዎች)፤ ከተራ፤ በዓለ-ጥምቀት፤ ዘመነ-አስተርእዮ፤ ፋሲካ፤ የዳስ በዓል፤ ታቦተ-ጽዮን፤ የጥር ሥላሴ፤ ቃና ዘገሊላ፤ ፍልሰተ ሥጋ፤ ፍልሰታ፤ ታውፋንያ፤ ኪዳነ-ምሕረት፤ ፳፱ ታኅሣሥ፡ ፪ሺ፱ (06/01/2017)

ልዑል እግዚአብሔር፡ በኢትዮጵያዊው ሥርዓት፡ጥር ፩ ቀን ለሚከበረው፡ ለ፳፻፱ (፪ሺ፱)ኛው ዓመት፡የሰላማችን የኢየሱስ መሲሕ ጥምቀት፣ እንዲሁም፡ ለተአምራዊው የቃና ዘገሊላ ሠርግ፥ ለመድኃኒታችን ድንግል-ማርያም ሰማያዊ ፍልሰትና ለኪዳነ ምሕረት በዓላት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅንነትና በሰላም አደረሰን!

ልዑል እግዚአብሔር፡ በኢትዮጵያዊው ሥርዓት፡ ጥር ፩ ቀን ለሚከበረው፡ ለ፳፻፱ (፪ሺ፱)ኛው ዓመት የሰላማችን የኢየሱስ መሲሕ ጥምቀት፣ እንዲሁም፡ ለተአምራዊው የቃና ዘገሊላ ሠርግ፥ ለመድኃኒታችን ድንግል-ማርያም ሰማያዊ ፍልሰትና ለኪዳነ ምሕረት በዓላት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅንነትና በሰላም አደረሰን!

የእናቲቱ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም እና የልጇ የወዳጇ የእግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕ በዓላተ-ትስብእት፡ በእርሱ፡ በታኅሣሥ ፩ዱ ቀን ተጀምሮ፡ በእርሷው፡ በታኅሣሥ ፯ቱ ቀን በኩልም ዐልፎ፣ የረቡዕና የዓርብ ጾምም እንኳ ሳይኖርበት፡ በፍጹሙ የጾመ-ማርያምነት መንፈሳዊ ደረጃ  እየተካኼደ፡ "ከተራ" እስከሚባለው፣ በአንዲት ቀን የጋድ ጾም እስከሚዘከረው፡ እስከጥምቀት ዋዜማ ቀጥሎ፡ በታኅሣሥ ፴ ቀን ያበቃል።

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...