ግዝረት፥ ኪዳነ-አብርሃም፥ እግዝእተብሔር፥ ጃንደረባ፥ ሄሮድስ፥ አይሁድ፥ ጻድቁ ዮሴፍ፥ መተጫጨት፥ ጃንደረብነት እና ድንግላዊነት። ፲ ህዳር ፳ሺ፱ ዓ.ም. (19 November 2016)

ቍጥር ፲፮/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

ግዝረትን፡ እንዲሁም፡ በእጮኛነት፥ ልጄን ወዳጄን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕንም፡ ከፅንሰቱና ከልደቱ፥ በጠቅላላም፡ ከሕፃንነቱ ጀምሮ፡ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት ያገለገለንን፡ ባለሟላችንን፡ ጻድቁ ዮሴፍን፥ በዚህ ተልእኮ፡ ከእርሱ ያልተለየችውን፡ የቅርብ አገልጋያችንን፡ ሰሎሜን ጭምር በሚመለከት።