ጾመ ፍልሰታ፥ ሱባዔ፥ ጾም፥ ምጽዋት፥ መለኮታዊ ቀዳሚ መልእክት፥ ድንግል ማርያም፡ ማን ናት?፥ ድንግል፥ እመ አርያም፥ እግዝእተብሔር እም፥ አነ፥ አነ እግዚአብሔር፥ እኔ፥ ንሕነ፥ ኢትዮጲስ፥ መልከ ጼዴቅ፥ ዐሠርቱ ቃላት፥ ንግሥት ማክዳ፥ ዓመተ ኪዳን፥ እመአርያም፥ መድኃኒት፥ መድኅን፥ እመ-እግዚአብሔር ጸባዖት፥ አስተርእዮ፥ ፍልሰታ። ሐምሌ ፴ ቀን፥ ፪ሺ፲ ዓ.ም. (06 August 2018)

ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፲ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] አሥረኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

ልዑል እግዚአብሔር፡ እንኳን፡ ለ፳፻፲ኛው (ሃያ መቶ [ኹለት ሺ] አሥረኛው) ጾመ ፍልሰታ ለማርያም፡ በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡ የምስጋና ሱባዔያችንን፡ ለመጀመር አበቃን!

እኛ፡ የዛሬዎቹ ኪዳናውያንና ኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች፡ ቸሩ ፈጣሪያችን፡ በሰማይም፥ በምድርም፡ በፍጥረተ-ዓለሙ ኹሉ ላይ በሰፈነችውና የእግዚአብሔርዋ መንግሥት በኾነችው ኢትዮጵያ አገራችን ውስጥ፥ በመላውም ዓለም ተሠራጭተን እየኖርን ባሳለፍነው የሕይወትና የጤንነት ህልውናችን፡ ዓመቱን ሙሉ አቆይቶን፡ እነሆ፡ ከዚህ የምስጋና ሱባዔያችን ለመድረስ አብቅቶናልና፡ እናመስግነው!

ይህችኑ፡ የዘንድሮዋን የፍልሰታ ጾማችንን፡ እንደተለመደው፡ እያንዳንዳችን፡ እንደየዓቅማችን፡ ስለራሳችንና ስለወገናችን፥ ስለአገራችንም ብቻ ሳይኾን፡ ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት ጭምር፡ በእውነተኛ ንስሓ ተመልሰንና በሱባዔ ተጠምደን፡ በምናካኺደው የምስጋና ጾም-ጸሎታችን የምንፈጽማት፡ በአዲሱ መለኮታዊ የዐዋጅ ቃል መንፈስና ዘመን ይኾናል።