በእስላሞች ሠይፍ ስለታረዱት ኢትዮጵያውያን የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል

በሊብያ አገር፡ በእስላሞች ሠይፍ ስለታረዱት ኢትዮጵያውያን፡ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል።

በአኹኑ ሰዓት፡ በሊብያ አገር፡
በእስላሞች ሠይፍ ስለታረዱት ኢትዮጵያውያን፡
ተጠያቂው ማን ነው? መፍትሔውስ ምንድር ነው?

ይህንኑ አስመልክቶ፡ ከደቡብ አፍሪቃው የግፍ ዕልቂት በኋላ፥ አኹንም ድረስ፡ በኢትዮጵያውያትና በኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ የ''እግዚኦታ'' እና ''ፈኑ እዴከ እምአርያም!''፡ ማለትም፡ ''እጅህን ከአርያም ላክ!'' የሚሉ፡ አሳፋሪና ዓመፀኛ
ጸሎቶችና ልመናዎች፥ ምልጃዎችና ምሕላዎች እንደቀጠሉ ይገኛሉ።