Archives

(ይህ ማብራሪያ የቀረበው፡ ይህን አርእስት በሚመለከት፡ ከዚህ በፊት፡ በተለያየ መልክ የተሰጡትን መግለጫዎችና የተላለፉትን መልእክቶች መሠረት በማድረግና በመከተል፥ በማስፋፋትና በማከል ነው።)

የጾመ ኢትዮጵያ (ነነዌ) መልእክትና ሥርዓተ ጸሎት።

በስመ እግዚአብሔር አብ፥ ወወልድ፥ ወመንፈስ፡ ቅዱስ፡ አሐዱ አምላክ፤
በስማ ለእምነ ወለንግሥትነ ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላከ፤
በኃይለ መስቀሉ፡ ለመድኃኒነ፥ ወለካህንነ፥ ወለንጉሥነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

 “ጾመ ኢትዮጵያ”

ተፈጸመ ትስብእት፡ በኢትዮጵያ ማርያም ድንግል!
በብሥራተ ቅዱስ ገብርኤል፡ ዜናዌ ቃል!

ይድረስ፡ ለኪዳናውያት እና ለኪዳናውያን፡ "የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ልጆች"፥ እኅቶቼና ወንድሞቼ፥ የክህነት ባልደረቦቼም!

ዮም ፍሥሓ ኮነ! በእንተ ርደተ መንፈስ ቅዱስ፡ ላዕለ ሓዋርያት፡ በጽርሓ ጽዮን ቅድስት!   

ይድረስ፦  ለኪዳናውያንና ለኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች! በያላችሁበት!  

ቅንን አስቡ!
እውነትን ተናገሩ!
መልካምንም አድርጉ!
እግዚአብሐርን መምሰል ይህ ነውና።

Think Right!
Speak The Truth!
Do Good!
This Is The Image of God.

ልዑል እግዚአብሔር፡
የዛሬ ኹለት ሺህ ሰባት ዓመት፡
በታህሣሥ አንድ ቀን፡
ባለሟሉን መልአክ፡ ቅዱስ ገብርኤልን፡
ወደቅድስቲቱ ኢትዮጵያዊት ድንግል ማርያም ልኮ፡
“ወናሁ ትፀንሲ! ወትውልዲ ወልደ!
ወትሰምይዮ ስሞ ኢየሱስ!”
ማለትም፡
“እንሆ ትፀንሻለሽ! ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ!

መስከረም አንድ ቀን፡ በርእሰ ዓውደ ዓመት፥
በድንግል ማርያም፡ በእናቲቱ ልደት፥
በኢየሱስ ክርስቶስ፡ ባምላክ ልጇም ትስብእት፥
የተወረሰውን ዓመተ ምሕረት፥
በአዳምና ሔዋን፥ የዓለሙን ፍጥረት፥
በቅዱሱ ኪዳን፡ የኢትዮጵያን ነጻነት፥
የተላበሱባት፡በእግዚአብሔርዋ መንግሥት፥
የኢትዮጵያ ሰዎች፥ ደግሞም ኢትዮጵያውያት፥
ባሉበት ቦታና በኑሮአቸው ዓይነት፥

ልዑል እግዚአብሔር፡
ከዘመነ ማርቆስ ወደዘመነ ሉቃስ አሸጋግሮ፡

የ፯ሺ፭፻፯ (የሰባት ሺህ አምስት መቶ ሰባተ)ኛውን ዓመት፡
የነጻነት ህልውናችንን በዓል፥

በመላው ዓለም ለሰፈነችው ኢትዮጵያና 
ለፍጥረቷ ሰላም፡ 
በዓመቱ መጨረሻ የምናካኼደውን፡ 
የምስጋናና የንስሓ ንኡስ ሱባኤያችንን፡ 
በዘንድሮዋም የ፪ሺ፮ ዓመተ ምሕረቷ ጳጉሜ፡
ልናደርግ፡ እነሆ ተዘጋጅተናል!
 ______________________

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።
የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

Pages